Fana: At a Speed of Life!

የለውጡ ዓመታት በጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው – አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የለውጡ ስድስት ዓመታት በጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት የለውጥ ዓመታት በዲፕሎማሲው መስክ የተከናወኑ ተግባራትን በማስመልከት ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በመድረኩም አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፤ ሀገራዊ ለውጡ የፖለቲካ ባህልን የቀየረ፣ የዲፕሎማሲ ጥረትና ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል።

ለውጡ በዲፕሎማሲ ረገድ በጋራ የመልማትና የትብብር ግንኙነትን ያጠናከረ ስለመሆኑም አንስተዋል።

በለውጡ ሂደት በውስጥና በውጭ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ቢኖሩም በጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ብለዋል።

ከገጠሙ ተግዳሮቶች አዳዲስ ዕይታዎችንና መንገዶችን አጉልቶ ማየት አስችለዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም ኢትዮጵያ ጠንካራ ሀገር ሆና እንድትዘልቅ አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያከናወነቻቸው ስኬቶች ከሀገር ልማት ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃም ስሟን ያስጠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል የሆነችበትና ሌሎችም የዲፕሎማሲ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመታት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም ሰላም ኖቤል ሽልማትም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው በመሆኑ በጉልህ የሚነሳ ነው ብለዋል።

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሰጠው ሽልማትም ከስኬቶቹ መከካል ይጠቀሳል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.