Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በግብርናው ዘርፍ ከጃፓን መንግሥትጋር በትብብር በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ከሆኑት ሂሮ ሺባታ ጋር መክረዋል፡፡

በምክክራቸውም በሩዝ፣ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና ልማት ላይ ከጃፓን መንግሥት ጋር በጋራ መሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በመስኖ ስንዴ ልማት የተገኘውን ስኬት አብራርተው ይህኑ ውጤት በሩዝ ለመድገም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚህም በሶማሌ ክልል 3 ሺህ ሄክታር መሬት ለመጀመሪያ ጊዜ በመስኖ ሩዝ ለማምረት መታቀዱን ጠቁመው÷ የመስኖ ሩዝ ልማትን ለማስፋት በሚደረገው ጥረት የጃፓን መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

በሩዝ፣ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቡና ልማት አነስተኛ ይዞታ ለላቸው አርሶ አደሮች በአቅም ግንባታ እና በግብዓት አቅርቦት ጃፓን እያደረገች ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.