Fana: At a Speed of Life!

የአካባቢ ብክለት ተጽዕኖ ባደረሱ 1 ሺህ 720 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት የአካባቢ ብክለት ተጽዕኖ ባደረሱ 1 ሺህ 720 ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ እንዳሉት÷ ባለስልጣኑ ባለፉት 9 ወራት 7 ሺህ 294 ተቋማትን ለመቆጣጠር አቅዶ 7 ሺህ 598 ተቋማት ላይ ክትትል ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
በተደረገው ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል በአካባቢ ላይ ብክለት ባደረሱ 1 ሺህ 720 ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ነው ያረጋገጡት፡፡
ከተቋማቱ መካከል 1 ሺህ 661ዱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን÷በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት ተግባራቸውን ሳያከናውኑ የቀሩ 59 ተቋማት መታሸጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ የአካባቢ ተጽእኖን ለመቆጣጠር በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት ተቋማት ህጎችን አክብረው እንዲሰሩ የጀመረውን ቁጥጥርና ክትትል አጠናክሮ መቀጠሉንም ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.