Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአካባቢ ብክለትን የመከላከል ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚያዝያ 2016 እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም የሚቆይ ክልል አቀፍ የብክለት መከላከል ንቅናቄ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ተጀምሯል፡፡

የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በዚሁጊዜ እንደገለጹት ÷በተለይ ከከተሞች ዕድገት ጋር ተያይዞ እየሰፋ የመጣው ፕላስቲክ የመጠቀም ልምድ በሰውና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።

ከፕላስቲክ ነፃ የሆኑ ሀገር በቀል ምርቶችን መጠቀም የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ወሳኝ በመሆኑ ዜጎች ትኩረት እንዲሰጡትም አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ ግዛቴ ግጄ በበኩላቸው ÷ በክልሉ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል በተያዘው ወር የተጣሉ ፕላስቲኮችን የመሰብሰብ ዘመቻ ይጀመራል ብለዋል፡፡

“ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚህ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በጥላሁን ሁሴን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.