Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የጋራ መግባባትን መፍጠር ይገባል – አቶ ብናልፍ አንዷለም

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ውይይትና የጋራ መግባባትን መፍጠር ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ።

የፌዴራልና የክልል ምክር ቤቶች በሀገር ግንባታ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የስልጠና እና የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በሰላም ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት እንዲሁም የክልል ምክር ቤቶች አባላት ታድመዋል።

የመድረኩ ዓላማ በሀገር ግንባታ ሂደት የሁሉንም ተሳትፎ የማጠናከር እንዲሁም በክልሎች ዘንድ የትብብር ግንኙነትን በማጎልበት ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ መሆኑ ተገልጿል።

የሰላም ሚኒስትሩ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ህግ አውጪ አካላት ህጎችን የማውጣትና አፈፃፀማቸውን የመከታተል ሃላፊነት ያለባቸው መሆኑን አንስተዋል።

የሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት ግንባታ ሂደት የሁሉንም ትብብርና ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ በዚሁ መልኩ ልንሰራ ይገባል በማለት ገልጸው፤ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ውይይትና የጋራ መግባባትን መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በየደረጃው ያለው አመራርና የህዝቡ ትብብር ታክሎበት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ በጋራ እንቁም ሲሉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር መግባባት ላይ መድረስ ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል።

የዋልታ ረገጥ እሳቤዎችን በመተው የጋራ ትርክቶች ላይ በማተኮር ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ከማያግባቡ ጉዳዮች ይልቅ የሚያቀራርቡ የጋራ ትርክቶች ላይ በማተኮር የጋራ ሀገራችንን እንገንባ ሲሉ ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.