Fana: At a Speed of Life!

የጉራጌ ህዝብ ሀገራዊ ለውጡ እውን እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል- አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ህዝብ ሀገራዊ ለውጡ እውን እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ገለፁ፡፡

በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ÷በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ምስረታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተ ህዝብ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የጉራጌ ህዝብ ፖለቲካዊ ለውጡ እውን እንዲሆን ፣ግቡን እንዲመታ እና የሪፎረም ስራዎች ስር እንዲሰዱ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን የበኩሉን ሲወጣ መቆየቱን አስገንዝበዋል፡፡

የጉራጌ ህዝብ በለውጡ መንግስት ራስን ችሎ በክልል የመደራጀት ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳደሩ÷የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክላስተር እንዲደራጅ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ይሁንና የክልል አደረጃጀቱን ያልተቀበሉ ቡድኖች ከውጭ እና ከውስጥ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ማህበረሰቡን የማይወክል ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

አሁንም የጉራጌ ህዝብ የለውጡን ጉዙ ለማፋጠን ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ÷ መንግስት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት ለዘላቂ ሰላምና ግንባት፣ለፖለቲካዊ ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.