Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡን ከተሳሳቱና ከተዛቡ መረጃዎች እንዲጠበቅ ብዙ መስራት ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ ከተሳሳቱና ከተዛቡ መረጃዎች እንዲጠበቅና ትክክለኛ መረጃዎች እንዲያገኝ ለማስቻል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበት ተመላከተ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመንግስት ኮሙኒኬሽን በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን÷ የተቋሙን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን በተመለከተም ከተቋሙ ሚኒስትር፣ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ተወያይቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ÷ ተቋሙ መንግስት የያዛቸውን የልማት፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎች አጀንዳዎችን የያዙ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እያከናወነ ያለው ስራ የሀገሪቱን ችግር የሚፈታ በመሆኑ የኮሚሽኑ አጀንዳዎች ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆኑ የተቋሙ ድጋፍ ወሳኝ ነው መባሉንም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)÷ ተቋሙ ሀገራዊ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በሀገሪቱ ካሉ የመንግስት እና የግል የሚዲያ ተቋማት ጋር እየሰራና ስራውንም እየገመገመ የማስተካከያ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ከተሳሳተና ከተዛባ መረጃ ይልቅ የመንግስት ትክክለኛ መረጃ የበላይነት እንዲያገኝና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራን ነው ያሉት ደግሞ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.