Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በመኸር እርሻ ከ169 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ይሰራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመኸር የእርሻ ስራ ከ169 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እንደሚሰራ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።

በክልሉ የግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር)÷በ2015/16 የምርት ዘመን 140 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል፡፡

በመጪው የምርት ዘመን ደግሞ የተሻለ ምርት ለማግኘት እንደሚሰራ አመላክተው በዚህም ክልሉ በ2016/17 የመኸር የምርት ዘመን 169 ሚሊየን 652 ሺህ 386 ኩንታል ምርት ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምርታማነቱን ለመጨመርም 8 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ለመጠቀም መታቀዱን በመግለጽ እስከአሁን 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ክልሉ መግባቱን ጠቅሰዋል፡፡

ከሚገኘው ምርትም 100 ሚሊየን ኩንታል ለምግብ ሰብሎች፣ 58 ሚሊየን ኩንታል ለአግሮ ኢንዱስትሪ የሚውልና 10 ሚሊየን ኩንታሉ ደግሞ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ነው ተብሏል።

በመኸር እርሻ ስራው ከ5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ እንደሚሸፍንም ተገልጿል፡፡

በከድር መሀመድ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.