Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ “የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል”ብለዋል።

በውይይታቸውም በቀጠናዊ የሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰው ሃይል ልውውጥ እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ተናግረዋል፡፡

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.