ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በማድሪድ ማራቶን ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶች አትሌት ምትኩ ጣፋ 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፍ ፥ ፍቅሬ በቀለ ተከትሎ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቋል፡፡
በሴቶች ማራቶን ደግሞ ቦንቱ በቀለ ሁለተኛ ስትዎጣ ፥ ቀበኔ ጫላ ሦስተኛ በመሆን ማጠናቀቃቸውን የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡