Fana: At a Speed of Life!

ለኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ወደ ሥራ ባልገቡት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፈቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ሥራ ባልገቡ ባለሃብቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

አቶ ኦርዲን ÷ በክልሉ ኢንቨስትመንት ለማጎልበትና ለማበረታታት የተሻለ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ልማት ሥራዎች በተለይም የወጣቱን የሥራ አጥነት ችግር የሚፈታ፣ ምርታማነትን የሚያጎለብት እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፉን የሚደግፍ መሆን ይገባል ብለዋል።

ሆኖም በክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድና መሬት ወስደው ወደ ልማት ያልገቡና መሬት አጥረው የተቀመጡ መኖራቸውን ጠቁመው÷ በዚህ ላይም እርምጃ እንደሚወሰድ አረጋግጠዋል፡፡

በክልሉ ሥራ ያቋረጡ ኢንዳስትሪዎችን ወደ ሥራ የማስገባትእና አምራች ኢንዳስትሪዎችን የመደገፍ ሥራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።

በክልሉ ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ላይ የተጀመሩ ህጋዊ እርምጃዎች መኖራቸውን ገልጸው÷ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት በማምጣት የክልሉን ገቢ በማሳደግ ረገድ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ባልገቡ የ8 ባለሃብቶች ደቃድ መሰረዙን እና ለ58ቱ ደግሞ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.