ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች እውቅና አገኙ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መስጠቱን አስታወቀ።
ቦርዱ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ በምዝገባ ሂደት ላይ ለነበሩ 9 ፓርቲዎች እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።
በዚህ መሰረት
1. አፋር ህዝባዊ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አህፍዴፓ)
2. አፋር ህዝብ ነጻነት ፓርቲ (አህነፓ)
3. ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)
4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሞዴፓ)
5. ቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)
6. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)
7. ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)
8. ዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) እና
9. ሱማሌ አንድነት ፓርቲ (ሱአፓ) ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ አግኝተዋል።