የብላክ ፓንተር ፊልም ኮከብ ተዋናይ ቻድዊክ ቦስማን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብላክ ፓንተር ፊልም ተዋናይነቱ ተቀባይነት ያገኘው አሜሪካዊው ተዋናይ ቻድዊክ ቦስማን በ43 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
ቻድዊክ ባጋጠመው የአንጀት ካንሰር ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡
ከሁለት አመት በፊት የወጣውና በላቀ ቴክኖሎጅ ላይ በተመሰረተው ብላክ ፓንተር ፊልም ላይ ቻድዊክ ቦስማን በቴክኖሎጅ የዘመነው ዋካንዳ መሪ ሆኖ ተውኗል፡፡
በፊልሙ ላይ ባሳየው ብቃትም በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ችሏል፡፡
ተዋናዩ ከአራት ዓመታት በላይ ካጋጠመው የአንጀት ካንሰር በሽታ ጋር ሲታገል መቆየቱ ይነገራል፡፡
ቻድዊክ ህይወቱ በመኖሪያ ቤቱ ማለፉም ነው የተነገረው፡፡
ህልፈቱን ተከትሎም በርካቶች ሃዘናቸውን እየገለጹ ይገኛል፡፡
ምንጭ፣ ቢቢሲ