በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን አለፈ
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን 200 ሺህ ማለፉ ተገለፀ።
ይህን ተከትሎም በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን 281 ሺህ 149 መድረሱን የወጡ ሪፖርቶች ያመላክታሉ።
በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30 ሺህ 667 ሲሆን፥ 1 ሚሊየን 13 ሺህ 909 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውም ነው የተነገረው።
ከአፍሪካ ከፍተኛ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች በመያዝ ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ድርሻውን ስትወስድ በሀገሪቱ 663 ሺህ 15 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 14 ሺህ 563 የሚሆኑት ለህልፈት ተዳርገዋል።
554 ሺህ 887 ሰዎች ደግሞ ማገገም ችለዋል ነው የተባለው።
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠልም ግብፅ፣ ሞሮኮ እና ኢትዮጵያ ተከታዩን ስፍራ ሲይዙ በግብፅ 99 ሺህ 425 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ነው የተባለው።
እንዲሁም በሞሮኮ 66 ሺህ 855 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲነገር 1 ሺህ 253ዎቹ ለህልፈት ተዳርገዋል።
ከሞሮኮ በመቀጠል ከአፍሪካ አራተኛ ደረጃን የያዘችው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 55 ሺህ 213 መድረሳቸውን እና ከዚህም ውስጥም 856 ሰዎች በቫይረሱ ለህልፈት መዳረጋቸውን ነው የጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው።
እንደ ወርልድ ኦ ሜትር መረጃ አሁን ላይ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ህክምና እየተከታተሉ የሚገኙት 232 ሺህ 729 ሰዎች ናቸው።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።