Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለ14 ሆስፒታሎች የደረጃ እድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የ14 ሆስፒታሎችን ደረጃ ማሳደጉን አስታውቋል።

በዚህም በክልሉ 12 ሆስፒታሎችን ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወደ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ሁለት ጠቅላላ ሆስፒታሎችን ደግሞ ወደ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማሳደጉን ገልጿል።

በክልሉ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የትግበራ ዘመን በጤናው ዘርፍ የለውጥ እቅድ 12 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችን ወደ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ሁለት ሆስፒታሎችን ደግሞ ወደ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማሳደግ በዕቅድ ተይዞ ሲሠራ መቆየቱን ጤና ቢሮው ገልጿል።

ጤና ቢሮው ከክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ጋር ባደረገው ምክክር ዝቅተኛውን የመመዘኛ መስፈርት ያሟሉ የሆስፒታሎችን ደረጃ ነው ያሳደገው።

ይህም በክልሉ የጤና አገልግሎቱን በተደራጀ፣ ጥራቱን በጠበቀ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

በዚህም ደባርቅ፣ መተማ፣ ሸጋው ሞጣ፣ ፍኖተሰላም፣ ቦሩሜዳ፣ መካነሰላም፣ ዓለም ከተማ እናት፣ አቃስታ (ህዳር 11)፣ ከሚሴ፣ መሃል ሜዳ፣ ላል ይበላ (የመቅደላ ጀግኖች መታሰቢያ) እና ተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታሎች ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወደ ጠቅላላ ሆስፒታል ያደጉ ናቸው።

ከዚያም ባለፈ ወልዲያ እና ደብረ ታቦር ጠቅላላ ሆስፒታሎች ደግሞ ከመስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማደጋቸውን ከክልሉ የጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.