Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ የአሜሪካ ወታደራዊ ‘የህዋ  ኃይልን’ በይፋ ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ወታደራዊ ‘የህዋ ኃይልን’ በትናትንትናው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ዶናንል ትራምፕ እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉትን ይህን የህዋ ሀይል በዋሽንግተን አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ሰፈር ላይ ነው ስራ ያስጀመሩት፡፡

በዚህ ወቅትም የህዋ ሀይሉን  “የዓለም አዲሱ የጦርነት ውጊያ ስርዓት” በማለት ገልፀውታል ፡፡

በሀገራዊ ደህንነት ላይ ከባድ ስጋት ባለበት በዚህ ወቅት የአሜሪካ የህዋ ሀይል የበላይነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ዘርፉን እየመራን ነው ነገር  ግን በበቂ ሁኔታ እየመራን አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ  በቅርቡ በብዙ ልዩነት ዘርፉን እንመራለን  ሲሉ በህዋ ሀይሉ የማስጀመሪያ ስነ ስዓት ላይ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የህዋ ጦር ሀይሉ ስጋቶችና ፀብ አጫሪ ድርጊቶች ለመከላከል እና አሜሪካ ከፍ ያለ  ቦታ ማግኘት እድትችል ያስችላታል ብለዋል፡፡

የህዋ ሀይሉ 16 ሺህ አካባቢ የአየር ኃይል እና ሲቪል ሰራተኞችን ያቀፈ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና ፀሀፊው ተናግረዋል ፡፡

የአሜሪካ ወታደራዊ ሀይል አመታዊ በጀት 738 ቢሊየን ዶላር ሆኖ የጸደቁ ሲሆን ለህዋ ኃይሉ የመጀመሪያ ዙር ግንባታ በዓመት 40 ሚሊየን ዶላር ወጪ ይደረጋል ነው የተባለው ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.