ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት የወሳኝ ኩነት አገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት የወሳኝ ኩነት አገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተዋል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በክፍለ ከተማው ወረዳ 09 በመገኘት የነዋሪነት መታወቂያ አሻራ በመስጠት የአገልግሎት አሰጣጡን መመልከታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክረተሪያን ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴም የነዋሪነት መታወቂያ አሻራ መስጠታቸውም ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በመገኘትም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።