Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ መርሀ ግብር በሶማሌ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሀ ግብር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተካሄዷል።

የሶማሌ ክልል የካቢኔ አባላት ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ መርሀ ግብርን ከረፉዱ 5:30 ላይ ለ1 ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር አሳይተዋል።

የክልሉ የካቢኔ አባላት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚውል 10 ሚሊየን ብር እና 2 ሺህ ፍየልና ሰንጋ ድጋፍ ማድረጋቸውን የሶማሌ ክልል ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.