በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ተሰጠ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚድያ አካላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በትግራይ እየተካሄደ ስላለው የሕግ ማስከበር ሥራና አስተዳደሩ በትግራይ ክልል ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
በጊዜያዊ አስተዳደሩም ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረብ በሕገ-ወጥ መንገድ የታሰሩ ሰዎች ጉዳይ እንደሚታይም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በትግራይ ክልል ያለውን የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚደርስ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።