ከተማ አስተዳደሩ “ለሀገር ልጅ የማር እጅ” በሚል በወቅታዊ ችግሮች ለተጎዱ ወገኞች የድጋፍ ማሰባሰብያ መርሃግብር የፕላቲኒየም ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ለሀገር ልጅ የማር እጅ” በሚል በወቅታዊ ችግሮች ለተጎዱ ወገኞች የድጋፍ ማሰባሰብያ መርሃግብር የፕላቲኒየም ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለድጋፍ መርሐግብር አዘጋጅ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
በከሃዲው የህውሀት እኩይ ስራ ጉዳት የደረሰባቸውን ንጹሃን ወገኖችን ለመደገፍ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የኪነጥበብ ባለሙያዎች “ሃገር ልጅ የማር እጅ” በሚል ከማለዳው ጀምሮ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ ።
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በድንገት በመገኘት ላቀረቡት ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ የፕላቲኒየም ደረጃ ድጋፍ አድርጓል ።
ምክትል ከንቲባዋም ይህንን ድጋፍ ስናደርግ የተጎዳው ወገን ከመላው ሃገር የተውጣጣ መሆኑን ተረድተን የህዝብ ጥሪ ምላሽ እንደሚያስፈልገው በማመን ነው ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።