Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከሃገር የሸሹና በሃገር ውስጥ የተደበቁ በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ መዘጋጀቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 1፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከሃገር የሸሹና በሃገር ውስጥ የተደበቁ በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ መዘጋጀቱን ገለፀ።
ተቋሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሳወቀው በዋናነት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ የሚያስችል የጥቆማ መቀበያ ስርአት እየዘረጋ ነው፡፡
ይህ እየተዘረጋ ያለው የጥቆማ መቀበያ ሰርአት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን በማጣራት ማስመለስ የሚያስችል ነው።
ተቋሙ በአሁን ወቅት በኢሜይል እና በነጻ የስልክ ጥሪ ጥቆማ መቀበል የሚያስችለውን አሰራር መዘርጋቱን አሳውቋል፡፡
ይህም በህገወጥ መንገድ በግለሰብ የተያዙ የህዝብ ሃብትን በሚሰጥ በወንጀል የተገኙ ሃበቶችን አጣርቶ ለማስመለስ ያሰችላል ተብሏል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.