ከተሞች በዓስር ዓመት ውስጥ 15 ሚሊዮን ምርታማና ተስማሚ የስራ ዕድልን ለመፍጠር ግብ መቀመጡ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተሞችን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ በዓስር ዓመት ውስጥ 15 ሚሊዮን ምርታማና ተስማሚ የስራ ዕድልን ለመፍጠር ግብ መቀመጡ ተገለጸ፡፡
የፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በከተማ ልማት ሴክተር የአስር ዓመትና የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ላይ በሀዋሳ ውይይት አካሄዷል፡፡
እቅዱን ያቀረቡት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል ለአስር ዓመት የተያዘው የዘርፉ ዕቅድ ዓላማው ከተሞችን የብልፅግና ማዕከላት ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በገጠርና በከተማ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ማስተሳሰር፣ የሀገራዊ ምርት ድርሻን በ73% ማሳደግ እንዲሁም ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢን በ2022 ዓ.ም 4,689 ዶላር ማድረስ የዕቅዱ ዋንኛ ግቦች መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም የከተሞችን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ በዓስር ዓመት ውስጥ 15 ሚሊዮን ምርታማና ተስማሚ የስራ ዕድልን ለመፍጠር ግብ ተጥሏል ብለዋል፡፡