Fana: At a Speed of Life!

በፖሊስና ህዝብ መካከል መተማመንን የሚፈጥር፣ ህዝብን ባለቤት ያደረገ፣ ዘመን ተሻጋሪ ፖሊስ መገንባት ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በፖሊስና ህዝብ መካከል መተማመንን የሚፈጥር፣ ህዝብን ባለቤት ያደረገ፣ ዘመን ተሻጋሪ ፖሊስ መገንባት እንደሚያስፈልግ ተነገረ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ሪፎርም አካል በሆነው የፖሊስ ዶክትሪን፣ ስታንዳርድና ማስፈጸሚያ ማንዋሎች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በሰላም ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማትና ስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሽሃንቆ ደለለኝ በጠሩት ስብሰባ ላይ የፖሊስ ዶክትሪን ዝግጅት ቡድን አባላት እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ የስዕብና ግንባታና ማልካም አስተዳድር ዳይሬክተር ኮማንደር ደረጄ አስፋው እና ጥናትና ሽታንዳርድ ዳይሬክተር ኮማንደር ዘካሪያስ ይርጋለም ተገኝተዋል።

በውይይቱ የኢፌዲሪ ፖሊስ ዶክትሪን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮሙፈሪሃት ካሚል እና የቀድሞው ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ተፈርሞ ከመስከረም 2013 ጀምሮ ወደ ስራ የገባ መሆኑ ይታወሳል።

ዶክትሪኑ የኢትዮጵያ ፖሊስ የሰው ሃብት ልማት፣ ስልጠና፣ አደረጃጀት፣ ግንኙነትና የተልዕኮ ማስፈጻሚያ ግብዓቶች በሙሉ መነሻና መድረሻእንዲሆን የሚጠበቅ ነው።

ከዶክትሪኑ ውጭ የሆኑ ፖሊሳዊ አገልግሎቶችና አፈጻጸሞች የማይፈቅድ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በውይይቱ ማጠቃለያ የሰላም ሚኒስትሯ አማካሪ ዶክተር አብዲ ዘነበ ዶክትሪኑ በፖሊስና ህዝብ መካከል መተማመንን የሚፈጥር፣ ህዝብን ባለቤት የደረገ፣ ዘመን ተሻጋሪ ፖሊስ የሚገነባበት ብቸኛ ሰነድ እንደሆነ ተናግረዋል።

ስለሆነም በቀጣይ በሰነዶቹ ላይ መላውን ፖሊስ አሰልጥኖ ወደ ስራ ማሰማራት እንደሚጠበቅ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ዶክትሪኑ ኢንተርፒስ (Inter-Peace) ከተሰኘ አለም ዓቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር በእንግሊዘኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሶማሌኛ፣ በትግርኛና፣ በአፋርኛ ተተርጉሞ ይሰራጫል ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.