Fana: At a Speed of Life!

በበዓል በእንስሳት እርድ ወቅት የሚተላለፉ በሽታዎች ለመከላክል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 27 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበዓል በእንስሳት እርድ ወቅት የሚተላለፉ በሽታዎች ለመከላክል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ ።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ÷መጭውን የገና በዓል አስመልክተው በዕርድ ወቅት የሚተላለፉ በሽታዎች እና የቆዳና ሌጦ ብክነትንና የጥራት ጉድለትን ለመከላከል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ዶክተር ፍቅሩ ህብረሰተቡ ለእርድ የሚሆኑ እንስሳትን ሲንመርጥ በተቻለ መጠን ምንም አይነት የበሽታ ምልክት የማያሳዪ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በግብይት ወቅትም ህብረተሰቡ እንስሳቱን ሲመርጥ የእንስሳትና የገንዘብ ንክኪና ቅብብሎሽ ስለሚኖር የኮረና ቫይረስ እንዳይስፋፋ ርቀትን በመጠበቅ እንዲሁም ሳኒታይዘር እና ማስክ በማድረግ ራስንና ህብረተሰቡን መጠበቅ ይኖርበታልም ነው ያሉት፡፡
እንስሳትን በቤት ውስጥ ማረድ ባይመከርም በቤት ውስጥ የምናርድ ከሆነ ጥሬ ስጋ ባለመብላት ከእንስሳት ወደ ሰው ከሚተላለፍ በሽታዎች እራሳችን እና ቤተሰባችን መከላከል እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል።
ከዚያም ባለፈ በከተሞች አካባቢ አራጀችን የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች አራጆች ከአንዱ ቤት ወደ ሌላ ቤት ስለሚንቀሳቀሱ የኮረና ቫይረስ እንዳይዛመት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እና ንፅህናን መጠበቅ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም በእርድ ወቅት ቆዳ እንዳይበሳሳ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሁም ጥሬ ቆዳና ሌጦ በአጭር ጊዜ ለብልሽት ስለሚዳረግ ምርቱን ወዲያውኑ ለሚያሰባስቡና ለሚያዘጋጁ ህጋዊ ነጋዴዎች/ወኪሎቻቸው/ ወይም ፋብሪካዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለፋብሪካዎች በማድረስ ለአገራችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲዉል ህብረተሰቡ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክትማስተላለፋቸውን ከየግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.