Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ር/መስተዳድር አቶ ሽመልስ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ህዝቡ ሲያከብር በመተሳሰብ ፣ በመከባበር እና በአብሮነት ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

እንዲሁም  ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብሩ ከኮሮና ቫይረስ እራሱን እየጠበቀ እና የመከላከያ እርምጃዎች እየወሰደ መሆን እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።

በበዓሉ ወቅትም የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.