Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲቲዩቱ ከሳተላይት የሚገኙ መረጃዎችን በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲያውል ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ስፔስ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ከሳተላይት የሚገኙ መረጃዎችን በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል እንዳለበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ፡፡

በምክር ቤቱ የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንስቲቲዩቱን የሥራ እንቅስቃሴ ለመገምገም የመስክ ምልከታ አካሄዷል፡፡

ኢንስቲቲዩቱ ከሳተላይት የሚገኙ በተለይም ተደክሞባቸው ለሀገር ፋይዳ ያላቸው መረጃዎች አጥጋቢ የግንዛቤ ሥራ ባለመሰራቱ ምክንያት ወደ ተጨባጭ ተግባር እየተቀየሩ አለመሆናቸውን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ እምዬ ቢተው ተናግረዋል፡፡

የስፔስ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሀገር ያለውን ፋይዳ በተመለከተ ለማሕበረሰቡ ከማስተዋወቅ አንጻርም ኢንስቲቲዩቱ ክፍተት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የባለሙያዎችና ተመራማሪዎችን አቅም ለመገንባት እና ጥቅም ለማስጠበቅ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል ፡፡

የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በ2020 በአፍሪካ ብቸኛዋ ሳተላይት ያመጠቀች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡

በቋሚ ኮሚቴው በኩል የተነሱ አስተያየቶች ትክክለኛ መሆናቸውንና የተጠቀሱትን ክፍተቶች በቀጣይ ለመፍታት እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.