Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለቀው ወጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለቀው ወጡ፡፡

ትራምፕ ላለፉት አራት አመታት የቆዩበትን ቤተ መንግስት በይፋ ለቀው የመጨረሻ ስንብታቸውን ወደ ሚያደርጉበት አምርተዋል፡፡

ከስንብታቸው በኋላም ወደ ፍሎሪዳ የሚጓዙ ይሆናል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ከባለቤታቸው ጋር ቤተ መንግስቱን ለቀው ሲወጡ፥ ምክትላቸው ማይክ ፔንስ በባይደን በዓለ ሲመለት ላይ ለመገኘት በስፍራው ቀርተዋል፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ ምሽቱን በይፋ ቃለ መሃል እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል፡፡

ወደ 25 ሺህ ወታደሮችም በዓለ ሲመቱን ያጅባሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.