Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የተገነባውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የተገነባውን የባንቆ ዳዳቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መረቁ፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በመጀመሪያ ዙር በሁሉም ክልሎች ካስገነባቸው 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከተገነቡት 3 ትምህርት ቤቶች አንዱ የሆነውን እና በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ የተገነባውን ትምህርት ቤት ነው ዛሬ የተመረቀው፡፡

ጽህፈት ቤቱ በክልሉ ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች 30 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ፣ በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ እና ደቡብ ኦሞ ዞን ሀመር ወረዳ ይገኛሉ፡፡

ዛሬ የተመረቀው ባንቆ ዳዳቱ መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተ ሙከራ፡ መማሪያ ክፍሎች እና ቤተ መጽሀፍትን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በደቡብ ክልል በሸካ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ያስገነባቸውን ቀሪ 2 ትምህርት ቤቶች በቅርቡ እንደሚያስመርቅ ይጠበቃል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.