Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከጤና ሙያ ማህበራት ጋር ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል- ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከጤና ሙያ ማህበራት ጋር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል ፡፡

ሚኒስቴሩ ከሙያ ማህበራቱ ጋር ምክክር ያደረጉ ሲሆን፤ ዶክተር ሊያ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የጋራ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የጤናውን ዘርፍ ለማሻሻል የተናጠል ስራዎች በቂ አለመሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትሯ ከጤና ማህበራት ጋር ጠንካራ ስራዎችን ለማከናወን መታቀዱንም ጠቁመዋል፡፡

በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የሙያ ማህበራት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ አበረታች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወናቸውም ተጠቁሟል ፡፡

ይሁን እንጅ ከሙያተኛው የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተግባራዊ ማድረግ ላይ ሰፊ ክፍተቶች ታይተዋል ነው የተባለው ፡፡

ከጤና ሙያ ማህበራት ጋር በመሆን በኮሮና ቫይረስ እና ሌሎች በሽታዎች ዙሪያ የተጀመሩ የጋራ ስራዎች እንዲያድጉ ትኩረት መሰጠቱንም አውስተዋል፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ እና ከተለያዮ የሙያ ማህበራት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች፣ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው ቸልተኝነት እንደ ሃገር ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል ፡፡

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.