Fana: At a Speed of Life!

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁለንተናዊ መልኩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እየተወጣ ነው- የደቡብ ክልል መምራን ማህበር

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁለንተናዊ መልኩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን የደቡብ ክልል መምራን ማህበር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የመራጮችና የሥነ-ዜጋ ትምህርት የአሠልጣኞች ሥልጠና ከዞን ልዩ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ መምህራን ማህበር አመራሮችና መምህራን በሶዶ ከተማ ለ3 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል፡፡
ዴሞክራሲን ባህላቸው ያደረጉ ሀገራት መሪዎቻቸውን የሚመርጡት ነፃ ፍትሐዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለውን ምርጫ በማካሄድ መሪዎቻቸውን በድምፃቸው ውክልና ይሰጣሉ ያሉት የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ÷ 6ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የመራጮችና የሥነ ዜጋ ትምህርት ለማስተማር ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅናና የምስክር ወረቀት አግኝቶ ወደ ሥራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
ይህንን ትልቅ ሀገራዊ አደራን በመወጣት ህዝቡ ይሆነኛል ብሎ የሚያምነውን ፓርቲ መሪ ማድረግ የሚችልበትና እምነት ያጣበትን በድምፁ በመወሰን ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር የሚደረግበት ሀገር ለመገንባት እንደሚሰሩም አመላክተዋል፡፡
የዴሞክራሲ ባህል የዳበረበትና ተወዳዳሪ ሀገር በምሥራቅ አፍሪካ እውን የማድረግ ራዕያችንን ተጠቅመን እውን ለማድረግ ዛሬ በእጃችን መዳፍ በሚገኘው እድል ተጠቅመን ዜጎቻችንን ማስተማር ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል አቶ ፍቅሬ ገ/ህይወት በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲበለጽግ የህዝቦች እኩልነት ነፃነት እንዲረጋገጥ ዜጎችን በማስተማር ማህበሩ የበኩሉን ድርሻ በመወጣቱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።
ለምርጫው ስኬታማነትም ተመሳሳይ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳሰበዋል፡፡
በአስጨናቂ ጉዱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.