Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የጣለችው የቪዛ ክልከላ የሃገራቱን የክፍለ ዘመናት ግንኙነት የሚሸረሽር ነው – የዳያስፖራ አባላት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የጣለችው የቪዛ ክልከላ ሁለቱ ሃገራት ለክፍለ ዘመናት የነበራቸውን የጠነከረ ግንኙነት የሚሸረሽር መሆኑን ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ፡፡
በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ውሳኔው አግባብነት የሌለው በመሆኑ ቆም ብሎ ማሰብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚጽፉ አምደኞችን ጨምሮ በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡
የ ጆ ባይደን አስተዳደር በተለያዩ ምክንያቶች ነው በሚል በኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎች ላይ የቪዛ ክልከላ መጣሉ ይታወሳል፡፡
ይህን አስመልክቶም የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ ክልከላው አግባብነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም አሜሪካ የሰብዓዊ ጉዳዮችን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም ማሰቧን በመጥቀስ አካሄዱ የተሳሳተ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለክፍለ ዘመናት የነበራቸውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የጠነከረ ግንኙነት የሚሸረሽር በመሆኑ ቆም ብሎ ማሰብ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ክልከላው ተገቢ እንዳልሆነ በመጥቀስም አሜሪካ ከአሜሪካ ካፒታል አመፅ አራማጆች ጋር ለመደራደር እንደማትችል ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስትም ከህወሃት ጋር እንዲደራደር ማስገደድ የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩልም የጆ ባይደን አስተዳደር የውጭ ፖሊሲ እርስ በራሱ የተጣረሰና ወጥነት የሌለው ነው ሲሉ አውስተዋል፡፡
የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ ከዚህ አንፃር ቀጠናዊ የፀጥታ፣የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አውስተዋል፡፡
እንዲሁም አንድነትን ማጠናከርና ቋሚ የሆነ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገድ ሊፈጠር ይገባል ነው ያሉት፡፡
ይህም በቀጣይ ሊፈጠር የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ጫናን መቋቋም እንደሚያስችል በመጥቀስ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.