Fana: At a Speed of Life!

ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ 850 ሚሊየን ዶላር ለመንግስት ገቢ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሰ) በኢትዮጵያ በግል የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ዘርፍ ለመሳተፍ ጨረታውን ያሸነፈው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ያሸነፈበትን 850 ሚሊየን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ለኢዜአ እንዳሉት በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት 14 ቀን ባልሞላ ጊዜ ድርጅቱ ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ ለመንግስት ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።

በዚህ መሰረት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ያሸነፈበትን 850 ሚሊየን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ኢንጂነር ባልቻ ገልጸዋል።

ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለጨረታው ማስኬጃ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት 500 ሚሊየን ዶላር ብድር አግኝቷል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ሁለተኛውን የቴሌኮም ኦፕሬተር ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.