የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከ640 በላይ የምርጫ ታዛቢዎችን ሊያሰማራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከ640 በላይ ታዛቢዎችን መልምሎ በመላ ሀገሪቱ ሊያሰማራ መሆኑን አስታውቋል።
በዚህም ጉባኤው ባለፉት ሳምንታት ለታዛቢዎቹ ሥልጠናዎችን መስጠቱን እና ለታዛቢነት የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ እና ከምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ባጅ ማሰራጨት መጀመሩን ገልጿል።
ኢሰመጉ ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት ባደረገቻቸው ምርጫዎች በታዛቢነት በመሳተፍ ያለበትን ኃላፊነት በብቃት ሲወጣ መቆየቱን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!