Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ስራ ዝግ እንዲደረግ አሳወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ከሃረሪና ከሶማሊ ክልል ውጪ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ስራ ዝግ እንዲደረግ አስታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት በእለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምጻቸውን እንዲሰጡ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር አዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሰረት ለመንግስታዊ እና ለማንኛውም መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል፡፡

በዚህም መሰረት

– ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል (ከሃረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) መንግስታዊ ተቋማት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ስራ ዝግ እንዲያደርጉ

– ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በክልሎች (ከሃረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) እና በፌዴራል የሚገኙ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ

– የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተእለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት..) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም::

– የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም ዜጎች ድምጽ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና እቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምጽ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.