Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 4 ሺህ 382 ካሬ መሬት ተረከበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዬጵያ መምህራን ማህበር ለሚያስገነባው ሁለገብ ህንፃ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ተረከበ።
መምህራን ማህበሩ የሚያስገነባው ህንፃ 2 ሺህ ካሬ ላይ የሚያርፍና 32 ወለል የሚኖረው ሲሆን 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ይፈጃል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለግንባታው የሚያስፈልገውን 4 ሺህ 382 ካሬ ቦታ ለማህበሩ በማስረክብ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ምክትል ከንቲባዋ ፕሮጀክትን መጨረስ ልምድ እንዳደረግነው ሁሉ ይህንን ህንፃ የአዲስ አበባን ውበት በሚጨምር መልኩ ለማጠናቀቅ ትብብር እናደርጋለን ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራን ማህበሩ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሃንስ በንቲ ላማህበሩ ስኬት ድጋፉ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በመድረኩ ለስራው ስኬታማነት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የከተማ አስተዳደሩ፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የመምህራን ማህበር አመራሮች እውቅና ስለመሰጠቱ ከትምህርት ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.