Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ 400 ኩንታል የእርዳታ እህል ወደ ግለሰብ መጋዘን ሲራገፍ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ከተማ 400 ኩንታል የእርዳታ እህል ወደ ግለሰብ መጋዘን ሲራገፍ ተያዘ።

የእርዳታ እህሉ መነሻውን ጅቡቲ አድርጎ በቀጥታ መቐለ አዋሽ ተብሎ ከሚጠራው መጋዘን መራገፍ ሲኖርበት በሁለት ግለሰብ መጋዘኖች ሲራገፍ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዟል፡፡


ከእርዳታ እህሉ ጋር የተሽከርካሪው ሹፌርና ረዳቱን ጨምሮ የመጋዘኑ ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

በመቐለ ሰሜን ክፍለ ከተማ ላጪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሁለት መጋዘኖች ሲራገፍ የተያዘው የእርዳታ እህል ትናንት ማምሻውን የገባ ነው፡፡

በትግራይ ክልል ከሳምንት በፊት በወጣ ሪፖርት ባለፉት ጥቂት ወራት ከ4 ሺህ 400 በላይ የእርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ነበር።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.