Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ አርሲ ዞን እስካሁን 1 ሚሊየን 48 ሺህ 391 ዜጎች ድምጽ ሰጥተዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን እስካሁን 1 ሚሊየን 48 ሺህ 391 ዜጎች ድምጽ መስጠታቸውን የዞኑ የምርጫ ቦርድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የምዕራብ አርሲ ዞን የምርጫ ቦርድ ምክትል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በቀለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በዞኑ በ11 የምርጫ ክልሎች 961 በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው ተካሂዷል።

በዞኑ የተመዝጋቢዎች ቁጥር 1 ነጥብ 1 ሚሊየን መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ ÷ ከእነዚህ ውስጥም 92 በመቶ የሚሆኑት ድምፅ መስጠታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የድምጽ አሰጣጡ በከተሞች አካባቢ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች እየተካሄደ ሲሆን÷ አብዛኛዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች ምሽት 12 ሰዓት ላይ ምርጫውን አጠናቀዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተዘዋውሮ በተመለከታቸው የዞኑ ከተሞችና አካባቢዎች ባሉ የምርጫ ክልሎችና ምርጫ ጣቢያዎች የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና የምርጫ ታዛቢዎች በተገኘቡት የድምጽ መስጫ ኮሮጆዎች ታሽገዋል።

የድምጽ አሰጣጥ ሁደቱን ያጠናቀቁ ምርጫ ጣቢያዎችም የድምጽ ቆጠራ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በምስክር ስናፍቅ፣ጥላሁን ይልማ፣ደበላ ታደሰና ያሬድ ሳህሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.