Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከሀረር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከሀረር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ የሰላም የፍቅር የመቻቻል ተምሳሌት የሆነችውን የሀረር ከተማን ሰላሟን ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላቱ የሚጫወቱትን ሚና አስመልክቶ ስለተደረጉ ክንውኖች መክረዋል፡፡
የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከተቋቋመ በኋላ በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎቸ ቀድሞ ከነበረው የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ከህብረተሰቡ ከመንግስት አመራሮች ጋር በመቀናጀት ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ክፍተቶችን በመለየት ሰላምን ከቤተሰብ ጀምሮ በመተግበር ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
የሰላም ቤተሰብ እና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች ከፀጥታ ቢሮ ጋር በመሆን ወደ ተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ገብተው መስራታቸው የሚመሰገን ተግባር መሆኑን ተሳታፊዎቹ
አውስተዋል፡፡
በመጨረሻም ሚኒስትሯ በሀረር ከተማ አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን የተደረገውን ውጤታማ ጥረት አድንቀው በዚህ ተግባር ለተሳተፉ የማህበረሰቡን ክፍል አመስግነዋል፡፡
በቀጣይ ይህንን እሴት አስቀጥሎ ለመጓዝ ሁሉም የየበኩሉን ሀላፊነት በመወጣት አስተማማኝ ሰላም መገንባት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.