Fana: At a Speed of Life!

የክልሉን ህዝብ የሚመጥንና ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ ስራ መስራት ይገባል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን ህዝብ የሚመጥን እና ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ ስራ መስራት እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልሽ አብዲሳ ተናገሩ፡፡
ጨፌው 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄደ የጀመረ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ያቀረቡትን የ2013 እቅድ አፈጻጸም ገምገሟል።
ከቀረበው ሪፖርት በመነሳት የምክር ቤቱ አባላት በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊና የመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፎች የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተዋል።
የመንገድ ተደራሽነት፣ የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ችግር እንዲሁም የትምህርትና ጤና ተደራሽነት ችግሮችን ጠቅሰዋል።
በክልሉ ከፀጥታ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመው በቀጣይ ልዩ ትኩረት እንዲደረግም የጨፌው አባላት አሳስበዋል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምክር ቤት አባላት የተነሱትን ችግሮች ለመፍታት በየደረጃው ያለ ዓመራር ትልቅ ሃላፊነት እንዳለበት አስረድተዋል።
የክልሉ አመራሮች ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው ለመፍትሄውም የመስራት ግደታና ሃላፊነት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
ለተነሱት ጥያቄዎች ሲመልሱ አመራሩ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛውን ኃላፊነት ሊወስዱ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በአባላቱ የተነሱት ችግሮች ቢያንሱ እንጂ አይበዙምያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ አመራር ይበልጥ ለመስራት ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩልም ርዕሰ መስተዳድሩ አመራሩ ህዝቡን የሚመጥን እና ተጠቀቃሚነቱን የሚያረጋግጥ ስራ መስራት እንደፈሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም የውጭ እና የውስጥ ጠላቶችን መመከት የሚቻለውም ህዝቡን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን መስራት ሲቻል ብቻ መሆኑን አውስተዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክልሉ 11 ሺህ የልማት ፕሮጀክቶች በ31 ቢሊየን ብር ወጪ ግንባታቸው ተጠናቁ ወደ ስራ መግባታቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለክልሉ ልማት በዘላቂነት ለማምጣትም የመንግስት በጀት፤ የግሉ ዘርፍ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ በተጣመረ መልኩ እንደሚመራ ገልፀዋል፡፡
በማህበራዊ ዘርፍ ፤ በገጠር ልማት እና በከተማ ልማት ዘርፍ ያሉ ስራዎች በተናበበ መልኩ እንደሚከናወኑም ነው የገለፁት፡፡
የጨፌው ጉባኤ በነገው እለትም ቀጥሎ እንደሚውል ይጠበቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.