Fana: At a Speed of Life!

አቶ እርስቱ ይርዳ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ 1 ሺህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል -አድሃ (አረፋ) በአልን ሲያከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ የተቸገሩትን በመርዳት እርስ በእርስ በመደጋገፍና ማዕድ በማጋራት በአብሮነት በአሉን ማክበር እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የህዝባችን የአንድነትና የአብሮነት በዓላት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ኢድ አል አድሃ/ አረፋ ተጠቃሽ ብለዋል፡፡
አረፋ ከሀይማኖታዊ ፋይዳው በተጨማሪ በህብረተሰቡ መካከል የመረዳዳት የመቻቻል እና የመከባበር እሴቶቻችን ይበልጥ የሚንጸባረቅበት መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን የገጠማትን የውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ጫና መመከት የሚቻለው ከምንጊዜውም በላይ አንድነታችንን ስናጠናክር ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በተለይ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሚደረገውን ትግል ልናጠናክር ይገባልም ሲሉ አብራርተዋል።
እኛ ከተባበርን እና ከተደጋገፍን ለየትኛውም ውስጣዊና ውጫዊ ጫና የማንበረከክ ታላቅ ህዝብና ሀገር ያለን ህዝቦች ነን ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይህችን ታላቅ ሀገር ወደ ብልጽግና ለማሻገር በተሰማራንበት ዘርፍ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.