Fana: At a Speed of Life!

ህይወቱን ለሚገብረው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት የምናደርገው ትንሹን አስተዋጽኦ ነው -የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
በከተማዋ ወጣቶች፣ጎልማሶች እና ሴቶች በደም ልገሳ መርሐ ግብሩ የተሳተፉ ሲሆን ለሀገር መከታ ለሆነውና ህይወቱን ለሚገብረው ጀግና መከላከያ ሠራዊታችን ይህ በጣም ትንሹ አስተዋጽኦ ነው በማለት ተናግራዋል፡፡
ለዚህ የህዝብ ደጀን ለሆነው ሰራዊት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማድረግ በሚችለው አቅም ሁሉ እገዛ ማድረግ አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ተሳትፏቸው በደም ልገሳ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን አገር አፍራሾች እስከሚከስሙ ግንባር ድረስ በዘመቻ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውንም ወጣቶች ተናግረዋል።
በደም ልገሳው የተሳተፉ ሴቶች በበኩላቸው ከዚህ የደም ስጦታ በተጨማሪ ስንቅ በማዘጋጀት አጋርነታቸውን ለመግለጽ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በፍሬው አለማየሁ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.