Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ከ 422 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የግንባታ ግብዓቶችን አምርቷል

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ422 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ለመንገድ ግንባታ ግብዓትነት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን ማምረቱን ገለፀ፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ካመረታቸው የግንባታ ግብዓቶች መካከል 142 ነጥብ 80 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የካባ ምርቶች፣ 85 ነጥብ 54 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የሲሚንቶ ውጤቶችና 193 ነጥብ 88 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የአስፋልት ኮንክሪት ውጤቶችን በራሱ አቅም አምርቶ ለተለያዩ የግንባታና ጥገና ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል ነው የተባለው፡፡
ባለስልጣኑ በ2013ዓ.ም በጀት ዓመት ውስጥ ያመረታቸው የግንባታ ግብዓቶች ከ2012ዓ.ም ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀሩ የ 5 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
የግንባታ ግብዓቶቹ በራስ አቅም መመረት መቻላቸው ባለስልጣኑ እያከናወናቸው ለሚገኙ የተለያዩ የግንባታና የጥገና ስራዎች የግብዓት እጥረት እንዳይፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን መገለፁን ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.