Fana: At a Speed of Life!

ሀሰተኛ ደረሰኝ ሲታተምባቸው የነበሩ 31 ህገ-ወጥ የካሽ ሬጂስተር ማሽኖች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሀሰተኛ ማንነት የሀገርንና የህዝብ ሀብት ለመዝረፍ ሲውሉ የነበሩ 31 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ማሽኖች ተይዘዋል፡፡

ደረሰኝ ግብይት መኖሩ የሚያረጋግጥ ለታክስ አሰባሰብ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ልውውጥ ሳይኖር ደረሰኝ መቁረጥ እና ማሰራጨት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሰረት የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ በያዛቸው ህገ-ወጥ ማሽኖች ብቻ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ዋጋ ያለው ግብይት ሳይኖር ግብይት እንደተፈፀመ ተደርጎ ደረሰኝ በመቁረጥ ለታክስ ስወራ እና ማጭበርበር ውሏል ተብሏል፡፡

በማሽኖቹ ታትመው የተሰራጩ ሀሰተኛ ደረሰኞች በአንዳንድ ግብር ከፋዮች ግብርን አሳንሶ ለማሳወቅ ጥቅም ላይ ሲውሉ እንደነበሩ መገለጹን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሀሰተኛ ደረሰኝ አሳትሞ በማሰራጨት ወንጀል ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ 26 ሰዎች ተይዘው ጉዳያቸው በህግ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ክትትል ተደርጎባቸው በግብይት ወቅት ደረሰኝ ያልቆረጡ 401 ደርጅቶች ተለይተው 20ሺህ 450 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን÷ በድርጊቱ ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ 532 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጉ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.