Fana: At a Speed of Life!

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የ1 ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ለመስጠት ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሀገር ለመከላከያ ለመስጠት ቃል ገቡ።
 
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅ እና ባዬ ፊዩል ኮርፓሬሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አመራርና ሰራተኞች ናቸው ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት ባደጉት ውይይት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል የገቡት።
 
እኛ የምንኖረው ሀገር ስትኖር ነው ያሉት አመራርና ሰራተኞቹ÷ ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሀይልን መመከት የሁሉም ሃላፊነት ነው ፤ አስፈላጊ ከሆነም ለመዝመት ዝግጁ ነን ብለዋል።
 
ትግሉ ከጁንታው ጋር ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ካሉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ነው ያሉት አመራርና ሰራተኞቹ÷ ብንሰደድ የሚቀበለን እንደሌለ በማሰብ የተቻለንን እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።
 
በተጨማሪም የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግና ደም ለመለገስም ቃል ተገብቷል።
 
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.