Fana: At a Speed of Life!

የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሻሸመኔ ግቢ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 178 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በቢዝነስ ትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ዛሬ ያስመረቀው፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አህመድ ከሊል የትምህርት ተቋሙ ከመማር ማስተማር ሂደት ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን እያከናውነ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የራሱን ከፍተኛ ድርሻ እንደተወጣ ዶክተር አህመድ ተናግረዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚንስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ደለሳ ቡልቻ ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያ ዘንድሮ የገጠማትን ችግር በእውቀታቸው በመታገዝ ለመፍታት ጥረት እንዲያደረጉ አደራ ብለዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ እና ለማ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevisi

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.