ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት መነሻውን ቻይና ያደረገውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል በዛሬው ዕለት አውጇል።
በዓለም ህዝብ ላይ ከፍተኛ ስጋትን በደቀነው እና ከ300 ሰዎች ለህልፈተ ህይወት ከዳረገው ቫይረስ ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ነው የተነገረው።
ጥንቃቄዎቹም፡-
1. በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ
2.ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ
3. የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣
4. እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣
እንዲሁም በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ደግሞ÷
- ወደሀገርበተመለሱበሁለትሳምንታትጊዜውስጥየመተንፈሻአካልህመም፣ትኩሳትናእንደሳልያሉየህመምምልክቶችካለብዎትወዲያውኑበአቅራቢያዎወደሚገኝጤናተቋምበመሄድአስፈላጊውንየህክምናአገልግሎትማግኘት፣
- የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት (14) ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረ ይህንንም ለጤና ባለሙያው ማስረዳት፤
- በሚያስሉበትናበሚያስነጥሱበትጊዜበሽታውወደጤነኛሰውእንዳይተላለፍአፍናአፍንጫንበክንድ፣በመሃረብወይምበሶፍትመሽፈን፣
- አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡
በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ ሀገራት ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድርግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።