Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከደቡብ ኮሪያ የደን ልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከደቡብ ኮሪያ የደን ልማት ሚኒስትር ኪም ጄይ ዩን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ሃገራቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት እና በደን ልማት ዙሪያ በትብብር ሊሰሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም የሃገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በዚህ ወቅት በኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራና ለረጅም ዓመታት የቆየ መሆኑም ተነስቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.