Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የህወሓት የሽብር ቡድን በከፈተው ጥቃት ከአካባቢያቸውና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ፡፡
የህወሓት የሽብር ቡድን በከፈተው ጥቃት በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች የእለት ደራሽ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በሀገር ላይ በከፈተው ጥቃት በርካቶችን ለከፍተኛ ችግር የዳረገ ሲሆን÷ በነዚህ መጠለያዎችም ነፍሰጡርና አራስ ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሴቶች፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች ይገኛሉ፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ ዜጎች ለዚህ ሊረባረቡ እንደሚገባም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.