Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የተበላሹ የአስፋልት መንገዶች ጥገና እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከባድ ዝናብ እና ረጅም ጊዜ በማገልገላቸው ለብልሽት የተዳረጉ የአስፓልት መንገዶችን የጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በዚህም ከዚህ በፊት ለፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ለመዘርጋት ሲባል ተቆፋፍሮ ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ የቆየውን ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ቤተ መንግስት በሚወስደው 450 ሜትር የሚሆን የአስፋልት መንገድ በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ላይ መደበኛ የጥገና ስራ አከናውኖ ለትራፊክ ክፍት ማድረጉንም ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ባለስልጣኑ÷ በአገልግሎት ብዛት ለብልሽት ተዳርገው የነበሩትን ከፍል ውሀ ዘውዲቱ ሆስፒታል እና ከሜክሲኮ አደባባይ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ድረስ የቀኝ መስመር የአስፋልት መንገዶች ጥገና አከናውኛለሁ ነው ያለው፡፡
በተያዘው በጀት ዓመትም ከ568 ኪ.ሜ በላይ ልዩ ልዩ የመንገድና የድሬኔጅ መስመሮችን ለመጠገን እቅድ መያዙን ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.