ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በቂ የፀጥታ ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ጥር 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በቂ የፀጥታ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በቂ የጸጥታ ጥበቃ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።
በጉባዔው ለመሳተፍ እና ጉባኤውን ለመከታተል የበርካታ ሀገራት እንግዶች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።
ስለሆነም እንግዶች በአጀብም ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይም አሽከርካሪዎች ቅድሚያ ለእንግዶቹ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።